የመጋቢያን ኮንፍረንስ 3ኛ ቀን

አንድ መሪ በሁለንተናዊ የሥነ ምግባር አቅጣጫ ሚዛኑን መጠበቅ እንዳለበት የገለጹት ዶ/ር ታሪኩ ፉፋ፣ መሪው በመንፈሳዊ፣በአእምሮአዊ፣በስሜታዊ፣ በማኅበራዊ፣በሥነ ልቦናዊና በገንዘብ ላይ የባለአደራነት ስሜትና ሃላፊነትን ካጣ የአገልግሎት መንገዱና ጉዞው በአጭር ይቀጫል ሲሉ ገልጠዋል።

ዲኖሚኔሽን ለአገልግሎት የተሰጠን ፕላት ፎርም እንጂ ቤተክርስቲያን አንዲት መሆንዋን ያሳሰቡት ዶ/ር በቀለ ሻንቆም፣ አንድነትን መጠበቅ፣ መረዳዳትን ማበልጸግ፣መደጋገፍን ማብዛት፣ አንዱ ሲጎዳ አብሮ መጎዳት፣የአንዱን ሃዘን ሌላውም የራሱ አድርጎ ማዘን፣ በዚህም የወንጌልን እውነት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለዓለም የማድረስ ሃላፊነትን በጋራ ከመሸከም ውጪ ቤተክርስቲያን የተለየ አጀንዳ እንደሌላት ተናግረዋል።

በጉባኤው ማሳረጊያ በጋራ የተመከረበት ባለ አስር ነጥብ የቃል ኪዳን ሰነድ በአቶ መኮንን ደሳለኝ አማካይነት የተነበበ ሲሆን፣ የፕሮግሪሙ ዋና አስተባባሪ የሆኑት የኅብረቱ ሚሽንና ቲዮሎጂ መምሪያ ዳሬክተር ፓ/ር ደረጀ ታፈሰ፣ በተለያየ መንገድ በዝግጅቱ ውስጥ በመሳተፍ ዋጋ የከፈሉትን ሁሉ በኅብረቱ ስም ካመሰገኑ በኋላ የኅብረቱ ፕሬዚዳንት ፓ/ር ፃድቁ አብዶ ባደረጉት የቡራኬ ጸሎት የጉባኤው ፍጻሜ ሆኗል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *